ማበር መተባበር ለድል!
ቢንያም ተስፋዬየሀገራችን ሁኔታ ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዳልሆነ እየሆነ መሄዱን የኢትዮጵያ ሕዝብ
ከተረዳው ቆይቷል ። ይህ ግንዛቤ በተመልካች ዘንድ ፣ ወደ ሌላ ድምዳሜ
እንዳያደርስ ግን በሁሉም ዜጋ ላይ ስጋት እየፈጠረ በመሄድ ላይ ነው ። ስጋቱ፣
የመጭው ትውልድ የዛሬውን ትውልድ " ባርነት የተስማማው፣ በህልሙ ድንጋይ
ይሸከማል " የሚል ወቀሳና ትችት እንዳያደስርበት ስለሚፈራ ነው። ነጻነትን የወረሰ
ትውልድ፣ የወረሰውን ነፃነት ለተተኪው ትውልድ ማውረሱ ቀርቶ፣ ባርነትን
ማውረስ ከፈቀደ ግን የተቀበለውን ባላመመለሱ ብቻ ሳይሆን፣ አደራ በመብላቱም
ጭምር፣ ከትውልድ ወቀሳና ከታሪክ ፍርድ ነፃ ሊሆን አይችልም።
የወቅቱ ትውልድ፣ የተተኪው ትውልድ ወቀሳና ትችት፣ ፍርድና ርግማን
እንዳይደርስበት ከፈለገ፣ መጀመሪያ ራሱን ነጻ አውጥቶ፣ የራሱን ነፃነት ለተተኪው
ትውልድ ማውረስ፣ የዜግነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን የታሪክም ተጠያቂነት እንዳለበት
ሊስተው አይገባም ። የመጀመሪያ አጣዳፊ ሥራ የሚሆነው፣ የራሱን ነፃነት አስከብሮ
መገኘቱ ይሆናል ። ይህንን ካላደረገ፣ ትርጉም ያለው ህይወት እኖራለሁ ብሎ ራሱን
ሊያታልል አይገባውም ።
ይህ በጠቅላላው አነጋገርና በመመሠረተ- ኃስቡ ፤ በአብዛኛው ዘንድ ተቀባይነት
ሊኖረው ይችላል ቢባልም፤ "ፍርድ ለግጫ" እስከሆነ ድረስ ግን ፣ ሰው የሌለውን
ያወርሳል ተብሎ አይጠበቅም። ምክንያቱም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የወረሰውን፣
በመነጠቅ ላይ ያለ ሕዝብ በመሆኑ ነው። የተነጠቀውን መልሶ በመንጠቅ በምሉዑነት
ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ ካልቻለ ግን ፤ ህይወቱ ብቻ ሳይሆን ኅልፈቱ የከፋ፤
ታሪኩ የተረሳ ሆኖ ይቀራል ። ታሪኩ መና ሆኖ እንዳይቀር ከፈለገ፤ አኩሪ ታሪክና
ነፃነት ያላትን ሀገር አውርሶ ማለፍ ይጠበቅበታል !
ዛሬ፣ መላው ሕዝባችን፣ ሀብት -ንብረትን፣ ምቾትንና ብልፅግናን፣ ሀሴትንና
ፍስሃን፣ ነፃነትንና ደሞክራሲን፤ ፍትኅ- ርትዕን፤ ኩራትንና በራስ መተማመንን፤
ወዘተ.. ለተተኪው ትውልድ ለማውረስ የሚያስችል ሁኔታን የሚያገኝ አልሆነም ።
እነኝህ ብቻ ሳይሆኑ፣ ትላንት የወራሳትን፣ ራሷን ሀገሪቱንም ቢሆን እንኳ፣ ዐይኑ
እያየ፣ ጆሮው እየሰማ እንደ ገና ዳቦ እየተቆራረሰች በመሄድ ላይ ነች። ታሪኳና
ባህሏ እየደበዘዘ እንዲጠፋ ሰፊ ዘመቻ በወያኔና ባዕዳን ተከፍቷል ።
የተረከባትን ሀገርና የሕዝቧን ታሪክ ሁሉ ሳይቀር ተነጥቆ እየጠፋበት ስለሆነ
ለተተኪው ትውልድ ሊያወርሰው የሚችል ቅርስ አይኖረውም ። የተነጠቀውን ውርስ
በማጣቱም፤ የሌለውን ያወርሳል ተብሎ አይጠበቅም ። እንዳልነበረች እየሆነች
የምትሄደውን ሀገር፤ ወደፊት ሀገር ትሆናለች ብሎ ተስፋ የሚያደርግ ዜጋ ስለሌለ፤
የጠፋችን ሀገር ለጠፋ ትውልድ ማስረክብ አይቻልም።
አጠፋፋችንና አሟሟታችን እንዳልሆነ ሆኖ የሚቀረውም በዚህ ምክንያት ነው። የውሃ
ሙላት እያሳሳቀ የሚውስደው ጅል ሰው ውሃው አይበላኝም ብሎ ስለሚዘናጋ
እንደተወሰደው ሁሉ፤ ሀገርና ሕዝብ ቀስ በቀስ እየጠፋ መሄዱን ቶሎ በጊዜ ተረድቶ
መፍትሄ ካልተገኘ ፤ ጠፍቶ ከጠፋ በኋላ ፤ ስለአጠፋፉ ስንክሳር ቢደረደር ከመጥፋቱ አይድንም።
"አወይ የኛ አሟሟት ፤ እንዳልሆነ ሆነ፤
መጥፋታችንን አውቆ ማንም ሳይነግረነ " እየተባለ ለአዝማሪ ቢያስገጥሙት፤ ከጸፀት
ማለዘቢያ አልፎ -ተርፎ የሚያመጣውዕርባና የለውም።
በመሠረቱ፤ የአምባገነን አገዛዝ ፤ አንዱ ከሌላው ይሻላል የሚባልለት ሥርዓት
ባይሆንም፤ " ከዝንጀሮ- ቆንጆ " መምረጥ ካስፈለገ ግን፤ ላለፉት አምሣ ዓመታትበኢትዮጵያከተፈራረቁትአምባገነኖችብቻሳይሆን፤የሌሎቹንሀገራት
አምባገነኖችንም ጭምር ሲታይ፤ እንደ ወያኔ የገዛ ሀገርን በፊርማ የቆረሰ፤
ሕዝብንም በዘር የከፋፈለ መሪ አልተገኘም ። በዕርግጥም፤ ወያኔ፤ ሀገርን ቆርሶ
በመስጠት ተግባሩ፤ ክብረ-ወስንን አግኝቷል ። በታሪክም፤ ሀገርን የሚሸጥና
ህዝብንም የሚበታትን ዘረኛ አገዛዝ ተደርጎ ተመዝግቧል ። በዓለም ዙሪያ በታሪክ
የተከሰቱና አሁንም ያሉ አምባገነን መሪዎች፤ በዘረጉት መራራ አገዛዝ ምክንያት፤
የሥልጣናቸው ተቀናቃኝ ይሆናል ብለው የሚጠረጥሩትን ሁሉ ፤ ደምስሠዋል ።
ብዙ ሕዝብ አጥፍተዋል ። የሀገር ሀብት- ንብረት አውድመዋል ። ነገር ግን፣ ሀገርን
ቆርሰው ሕዝብን በታትነው አልተገኙም። እንዲያውም፣ ከራሳቸው ሀገር አልፈው-
ተርፈው፤ ተጨማሪ ግዛት ለማምጣት ሲጥሩ ኖረዋል። ይህ ሀቅ ነው ወያኔን ልዩና
ከይሲ፣ ወራዳና ከሀዲ የሚያደርገው።
አንዳንድ ዋልጌ ተኳሽ፤ ጥይቷን " ፈልገሽ ምች " ብሎ አንደሚተኩሳት፤
ወያኔዎችም ፤ ህገ መንግሥት እንዲባልላቸው የፈለጉትን ቀርፀው፤ ሕዝቡን ወደ
ፈለግኽው ሂድ ብለው በተጨባጭ ግን ሁሉንም አፍነው እየገዙ አሉ ።አንቀጽ 39
ለወያኔ የቀውጢ ቀን ግንጠላ የተዝጋጀች ናት ። ሌሎች አምባገነኖች ግን፤ ህግ
አውጥተው ህዝባቸውን በአዋጅ አልበታተኑም። ሀገራችውን በፊርማቸው አፅድቀው
አልቆራረሱም ። ይህንን በታሪክ፤ በትውልድና በህግ የሚያስጠይቅ አሳፋሪ ተግባር
የሰራው ወያኔ ነው ።" ከበሽታ ሁሉ ፈንጣጣ ክፉ ነው ፤
ክትባት እንዳንች የሚያምርበት ማነው ? " የሚባል ቅኔ ጥንት የሰማ ነበር። ዛሬደግሞ፤"ከአምባገነንአገዛዝየከፋውየቱ ነው?ሌላውን ማን አውቆ መልሱ ወያኔ ነው።"
ይህ ሀቅ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ዘወትር፤ ስለወያኔ ተግባርና ምንነት ብቻ ቢያነሱ
ቢጥሉት፣ በትግሉ ሂደት ላይ ያመጣው ለውጥ አለመኖሩን መረዳት አስፈላጊ
ይመስለናል ። ተወደደም ተጠላ፤ እስካሁን የተደረገው ህዝባዊ ትግል፤ የታሰበውን
ውጤት ሊያስመዘግብ አልቻለም ። ይህንን ሀቅ ሊቀበል ያልተዘጋጀ ካለ፤
ያስመዘገበውን ውጤት እንዲያመለክት ይጠበቅበታል።
እንዲያውም፤ ዕውነቱ ፍርጥርጥ ተደርጎ መነገር ካለበት፤ ተቀዋሚው ኃይል፤
እስካሁን ድረስ ሲያደርገው የቆየው፤ ባመዛኙ ማለት ይቻላል፤ ወያኔ በሚጥልለት
አጃንዳ ዙሪያ ከመሽከርከር ያለፈ እንቅስቃሴ አይደለም ። በራሱ አነሳሽነትም፤
የራሱን የትግል አጀንዳ በጋራ ነድፎ፤ በራሱ የትግል እንቅስቃሴ ዙሪያ ሕዝቡን
ሊያሰማራ የሚችል ህዝባዊ ኃይል ሊፈጥር አልቻለም ። ህዝባዊ ኃይል ከሌለ
ደግሞ፤ ሕዝባዊ አመፅ ማምጣት አይቻልም ። ያለ ሕዝባዊ አመፅ፤ አምባገነን
አገዛዝን ማስወገድ ያስቸግራል ።
በጥቅሉ የአፍሪካን አገሮች ብንመለከት የመረረ የነጻነት ትግል የተካሄደባቸው ደቡብ
አፍሪካ፣ ኬንያ፣ አልጂርያ፣ ዚምባብዌ ናቸው፤ እንደሚታወቀው እነዚህ አራቱም
አገሮች ለአውሮፓውያን ሰፈራ የታጩ ነበሩ፤ ምናልባት በእነዚህ ዘገሮች ለነጻነት
የተደረገውን ትግል መራራ ያድረገው ዋናው ምክንያት አፍሪካውያኑ አገር-አልባሆነው
እንዳይቀሩ የነበረው ስጋት ሊሆን ይችላል፤ በአንጻሩ ሱዳን የነጻነት ትግል
አልነበረም፤ የኢትዮጵያ ጎረቤት ስለሆነ ቶሎ ነጻነትን በመስጠትና ወዳጅ
በመፍጠር፤ በሶማልያም በኩል እንዲሁ ቶሎ ነጻነትን በማሸከም ምዕራባውያን
ወደፊት ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት እየቀረጹ ነበር ለማለት ይቻላል፤
ግብጾች ከስንት ሺህ ዓመታት በኋላ ነው አሁን በዘመናችን ወንዶችና ሴቶች
በአደባባይ ወጥተው እምቢ! በማለት ሙባረክን ያስወረዱት! ለነጻነት የመታገሉ
ልምድ ስለሌላቸው፣ በዚያም ላይ ባህልና ሃይማኖት ተጨምሮበት ሙባረክን
አስወርደው ነጻነትን አላገኙም፤ እንደዚሁም የኢትዮጵያ ሕዝብም አጼ ኃይለ ሥላሴን
አስወርዶ ነጻነቱን አላገኘም::
እያንዳንዱ ሰው የተፈጠረው ከነፍላጎቱና ፍላጎቱን ለማሟላት ካለው አዛዥነት ጋር
ነው፤ ባርያ ፍላጎቶቹን ለማሟላት አዛዥነቱ የለውም፤ አዛዡ የራሱ ፈቃድ ነው፤
የራሱ ፈቃድ የሌለው ሰው ወና ሰው ነው፤ ዋናውን የሰውነት ባሕርዩን ያጣ ባዶ
ዕቃ ነው፤ ከባዶ ዕቃ ውስጥ የሚወጣ ነገር የለም፤ ለዚህ ነው ለነጻነቱ መታገልና
በራሱ ጥረት ድልን ለመጎናጸፍ የማይችለው። ይህንን ለመርታት እና ድል ለማድረግ
በቅድሚያ ሀገራችን ኢትዩጵያን ሲቀጥልም ደግሞ ለጎረቤት ሀገሮች ሳሌ ለመሆን
ትልቁ መፍትሔ እና መንገድ ለአንድ አላማ በአንድነት ጠላታችን የሆነውን ወያኔን
ከስልጣን ላይ ማስወገድ ፥ ለዚህም ክንዋኔ ስኬት በህብረት በአንድነት በእኩልነት
መቆም መታገል!!!
ኢትዩጵያ ለዘላለም ትኖራለች!
ቢንያም ተስፋዬ
No comments:
Post a Comment