የኦሮሚያ ክልል ውሎ እና የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ ስኬት

በተልይ የትራንስፖርት ኣገልግሎት የሚሰጡ ኣውቶብሶች መናሕሪያዎችን ጭር ያደረጉ ሲሆን ትራፊኮች ታርጋ በመፍታት ሲወስዱ ተስተውለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሕወሓት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ጨምሮ የተለያዩ በስራ ላይ ለመሰማራት ሲያሽከረክሩ የተገኙ አውቶብሶች እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን መንገዶች በተለያዩ ኣከባቢዎች ተዘግተው መውጫና መግቢያ ኣልነበረም፥ የግብይት ማቆም ኣድማው ለሚቀጥሉት ቀናት እንደሚካሄድ ይታወቃል::

ስለዚህ በዚህ ኣድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት ክልክል ነው። እቃዎችን ጭነው በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም አቀናጆች አስታውቀዋል። የመኪና ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች እና ነጋዴዎች ይህንኑ አውቀው ይህን የአድማ ወቅት በማክበር ለህዝብ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ እና ንብረታቸውንም ከውድመት እንዲያድኑ ደግመን እናሳስባለን። #ምንሊክሳልሳዊ








No Kchat in Jijiga City





No comments:
Post a Comment