Tuesday, March 10, 2015

”ማርች 8” እና ኢትዮጵያዊቷ ሴት ዛሬ! – ጉዳያችን


ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረብያ ስደት ላይ
Ethiopian Women in Soudi”ኢትዮጵያዊቷ ሴት ለየት ያሉ ባህርያት አላት። በቅዱሱ መፅሐፍ ላይ ሙሴ ህዝበ አስራኤልን ይዞ ከ ግብፅ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲገባ በስራው ሁሉ የምትረዳው እና ለትዳሩ አጋር ያደረገው ኢትዮጵያዊቷን መሆኑን በቅዱስ መፅሐፍ ውስጥ ማንበቤን አስታውሳለሁ። ‘በምድር ከሚነሱት ነገስታት ማንም ያንተን ያህል ጥበብም ሆነ ሀብት አይኖረውም’ የተባለው ንጉስ ሰለሞን ልቡን ከፍቶ የሆዱን ያወራው ከ ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ (አዜብ) ጋር ነው። ኢትዮጵያውያን ሴቶች ልዩ ናቸው። ክብራቸው፣ዝምታቸው፣እርጋታቸው እና አስተዋይነታቸው ሁሉ የተለየ ድባብ ያላብሳቸዋል ።አዲስ አበባ ለስብሰባም ሆነ ለተመሳሳይ ሥራ ስሄድ ከምገባበት ኬክ ቤት ጀምሮ አስከ አየር መንገዳችሁ አስተናጋጆች ድረስ ያሉት ሴቶችሁ ልዩ፣አስተዋይ እና ብሩህ አእምሮ አላቸው።” ካምፓላ ውስጥ በሚገኘው ”ማካራሬ” ዩንቨርስቲ ውስጥ የ ልማት ጥናት ፕሮፌሰር ዩጋንዳዊው ማተምቤ ናቸው። አዎን ከተናገሩት ውስጥ አንድም የሚጣል እንደሌለው አውቃለሁ። ያንን ንግግር ዛሬ ላይ ሆኘ ሳየው በተለይ” ማርች ስምንት የሴቶች ቀን ታስቦ ዋለ” የሚለው ከኮሚንስቶች ፕሮፓጋንዳ ያላለፈ፣ የወረቀት እና ንግግር ማሳመርያ ዜና መሰል ነገር ከወደ ሀገር ቤት ስሰማ ያስገርመኛል።ይህ ማለት ግን ”ማርች” ስምንት የሴቶች ቀን መከበር የለበትም የሚል ሃሳብ የለለኝ መሆኑን እንዳትዘነጉብኝ።አከባበሩ አንዳች የረባ የሴት እህቶቻችንን ሕይወት የሚያሻሻል ሥራ ተሰርቶ ቢሆን ጥሩ ነበር።ሁኔታው ተቃራኒ ሆኖ ሳለ ስለ በዓሉ ማውራት በራሱ በሴት እህቶቻችን ላይ ከመቀለድ አይተናነስም።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ( UNHCR) ሰኔ 27/2011 አንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ”በ 2011 የ ሰዎች ዝውውር በ ኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ባወጣው ሪፖርት ላይ አንዲህ የሚል ሰፍሮ ይገኛል-
”Young women, most with only three to four years of primary education, from various PARTS of Ethiopia are subjected to domestic servitude throughout the Middle East, as well as in Sudan, and many transit through Djibouti, Egypt, Libya, Somalia, Sudan, or Yemen as they emigrate seeking work. Some women become stranded and exploited in these transit countries, unable to reach their intended destinations. Many Ethiopian women working in domestic service in the Middle East face severe abuses indicative of forced labor, including physical and sexual assault, denial of salary, sleep deprivation, and confinement. Many are driven to despair and mental illness, with some committing suicide…..” 1
”ከ ሦስተኛና አራተኛ ክፍል ያልዘለሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መጥተው ጅቡትን፣ግብፅን ፣ሊብያን፣ሶማልያን፣ሱዳንን ወይንም የመንን አቁአርጠው ወደ መካከለኛው ምስራቅ የ አረብ ሃገራት ለመሄድ ይሞክራሉ።ብዙዎች ገና እነኝህን ሃገራት ሳይሻገሩ እዝያው ጉልበታቸውን ሸጠው እንድያድሩ ያረጋቸዋል….በመካከለኛው ምስራቅ በሥራ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በ ከባድ የ ጉልበት ሥራ፣የ አካልና የ ፆታ ጥቃት፣የለፉበትን የመነጠቅ ወዘተ ይፈፀምባቸዋል።በእ ዚህም ምክንያት ብዙዎች የ አአምሮ ህመም ደርሶባቸው እራሳቸው ያጠፋሉ….”
”እማዬ ለምን ወለድሽኝ ?”
Ethiopian in Saoudiዛሬ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ እህቶቻችን በሊባኖስ፣ሳዑድ አረብያ፣የተባበረው አረብ አምረት፣ኩዌት፣ወዘተ በቤት ውስጥ ሥራ እና በተለያዩ አስከፊ ተግባራት ተሰማርተው ይገኛሉ።አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ እህቶቻችን ለአረብ ሀገር እንግልት ሲሳፈሩ ያገኛሉ። ይህ ብቻ አደለም በቅርቡ በአዲስ አበባው ራድዮ እንደተገለፀው ወደ አረብ ሀገር የሚያሰድዱት ደላሎች ከ ከተሞች ይበልጥ ሰፊ የመገናኛ መረባቸው በገጠር ውስጥ መሆኑ እና ለምሳሌ በወሎ ውስጥ በምትገኝ የአንድ ገበሬ ማህበር መንደር ውስጥ ለ ማህበራዊ ጉዳይ ከተሰበሰቡት ገበሬዎች ለ ናሙና በተወሰደ መረጃ ከ ሃምሳ ገበሬዎች ውስጥ ሰላሳ ሁለቱ ልጆቻቸውን ለ አረብ ሀገር እንግልት መላካቸውን ገልፀዋል። ከእዚህ ሁሉ አሳዛኙ ነገር ደግሞ ሁሉም የ ሴት ልጆቻቸውን ወሬ ሰምተው የማያውቁ መሆናቸውን ና ግራ መጋባታቸውን በለቅሶ መግለፃቸው ነው ። የ እህቶቻችን ጉዞ በ አየርመንገድ ብቻ የምመስለን ካለን በጣም ተሳስተናል። በ እዚሁ የ ራድዮ ዘገባ መሰረት ባለፉት አምስት ወራት ብቻ በ ሱዳን በኩል የወጡት እህቶቻችን ብዛት በ ብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠር መሆኑም ተነግሯል።
በ አረብ ሀገር ያሉት እህቶቻችንን መከራ ና ስቃይ መተንተን በ ቃላት መቀለድ ሆነብኝ።ከፎቅ ላይ እራሳቸውን የወረወሩትን፣መርዝ የጠጡትን፣የፈላ ውሃ የተደፋባቸውን፣ምግብ ሳይበሉ በረሃብ ጠኔ ሕይወታቸው ያለፈውን፣እስር ቤት ተወርውረው ተረስተው የሞቱትን፣ ኩላሊታቸው የቀዶ ጥገና ሕክምና አዋቂ ባልሆኑ ሰዎች ወጥቶ የተወሰደባቸውን (ከዓመት በፊት ‘ሲ ኤን ኤን’ የተሰኘውን የ አሜሪካ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያውያን እህቶቻችን የኩላሊት መወሰድ ላይ ያሳየውን ዘገባ ልብ በሉ) እህቶቻችን ዛሬም ”እማዬ ለምን ወለድሺኝ?” እያሉ ነው።መከራን የምንረዳው እኛ በዝያ መከራ ውስጥ ተገብተን አልያም በእህታችን ወይንም በሴት ልጃችን ላይ ደርሶ ቢሆንስ? ብለን ስናስብ ብቻ ሊሆን ይችላል።
ኢትዮጵያዊት ሴት በአረብ ሃገራት ውስጥ የተዋረደችውን ያህል በታሪካችን የተዋረደችበት (ውርደቱ የ አኔም፣የናንተም፣የሁላችንም መሆኑን ሳንዘነጋ) ጊዜ ነበር ለማለት አያስደፍርም ።በአረባውያኑ ምድር ኢትዮጵያውቷን ሴት አይዞሽ ባይ ማጣት፣ግራ መጋባት፣ተስፋ መቁረጥ፣ግፍ እና መከራው አንገላተዋት ባዶ አውላላ ሜዳ ላይ የቀረች ብቸኛ ፍጥረት የሆነች ያህል እየተሰማት ያለችበት ጊዜ ነው።
142398998551ሀገሮች በድንበር መካለል ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በመካከላቸው የሚኖረውን ግንኙነት ከንግዱ ዘርፍ ባለፈ የ ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር ሌላው የሚያገናኛቸው ጉዳይ ነው። ይህ ግንኙነት ደግሞ ዲፕሎማስያዊ ግኑኝነት እንድያዳብሩ ትልቅ በር ከፍቷል ። ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት በ ዘመናት ውስጥ የራሱን አድገት አያሳየ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሰናል።የ ዲፕሎማሲ ግንኙነት አጅግ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ሲሰራበት የነበረውን ዘመን አልፎ ዛሬ ”public diplomacy” ”ግልፅና ሕዝቡን መሰረት ያደረገ” የ ዲፕሎማሲ ዘመን ላይ እንገናኛለን። የ ሀገሮችን የ ዲፕሎማሲ ግንኙነት መልክ ለማስያዝ ና ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በሁዋላ በ ሀገሮች መካከል የነበረውን ግንኙነት መልክ ያስያዘው ብሎም የ ዓለም አቀፍ ሕግን ቅርፅ የሰጠው አሁንም ድረስ በሥራ ላይ የሚገኘው የ ዲፕሎማሲ ሕግ የ” ቬና ኮንቬንሺን ” (የ ቬና ውል ) ይባላል። ይህ ውል በ ሚያዝያ 18/1961 እንዳውሮፓውያን አቆጣጠር ወጥቶ በ ሚያዝያ 24/1964 አሁንም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ሥራ ላይ ዋለ። በ አውሮፓውቷ ሀገር ኦስትርያ ዋና ከትማ ቬና ውሉ ሲፈረም ከፈረሙት ሀገሮች አንዷ በወቅቱ አብዛኛዎቹ የ አፍሪካ ሀገሮች በ ቅኝ ግዛት ስር በሆኑበት ዘመን ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን የ ውሉ ቀዳሚ ፈራሚ ብቻ ሳትሆን በ ማርቀቅ ሂደቱም ሁሉ ተሳታፊ ነበረች።ዛሬ ግን የእዚህን ውል ዋና አካል የሆነውን አንቀፅ ሶስት የ አትዮጵያ መንግስት ከነመኖሩም የዘነጋው ይመስላል።
የ ቬና ውል አንቀፅ ሶስት ”b” አንዲህ ይላል-
Article 3
1.The functions of a diplomatic mission consist, inter alia, in:
(a) Representing the sending State in the receiving State;
(b) Protecting in the receiving State the interests of the sending State and of its nationals, within the limits permitted by international law; 2
”የ አንድ ሀገር የ ዲፕሎማሲ ሉዑክ አንዱ ተግባር በ ተቀበለው ሀገር ውስጥ የ ሃገሩን ጥቅሞች ና የ ዜጎቹን ጥቅሞች የ አለማቀፍ ሕግ ማቀፍን በተከተለ መንገድ ማስከበር” ነው ይላል።
የሀገራችን የወቅቱ የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስት አባልነትን መሰረት ያደረገ እና ቅድምያ ለመንግስት ታማኘትን ማእከል ያደረገው የሀገራችን ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ስርዓት በመካከለኛው ምስራቅ ለሚሰቃዩት እህቶቻች በቁስል ላይ ቁስል ሆኖባቸዋል።
ዛሬ ለ እህቶቻችን በሄዱበት ሀገር መብታቸውን ለማስከበር ኃላፊነት ያለበት መንግስት መሆኑን የሚዘነጋው አይኖርም ።ይህ ደግሞ በ አለማቀፍ ሕግ እንደ መንግስት ተቁአምነት ግዴታው ነው።የአንድ መንግስት ቀዳሚ ተግባር የ ሃገሩን ሉዓላዊነት ከማስከበር ጀምሮ የ ዜጎቹን ደህንነት (ዜጎቹ በየትኛውም የ ምድር ማአዘን ቢኖሩ) ማስጠበቅ ነው። አሁንም ይህ ኃላፊነት በቀጥታ የምመለከቷ መንግስትን ነው።መንግስት በ አረብ ሀገር እንባዋን የምታፈሰውን ኢትዮጵያዊት ሴት ለመርዳት የወሰደው አርምጃ ትንሿ ጅቡቲ በ ዲፕሎማሲ ተልኮዋ ከምትሰራው ሥራ ያነሰ ነው ሲሉ ብዙዎች ይተቻሉ።ይህም ተራ በስሜታዊነት የተሞላ ነቀፋ ሳይሆን በ ገሃድ የታየ እውነታ ነው። በ ሶርያ፣ሊባኖስ፣ሳዑድ አረብያ፣ሱዳን የነበረውን ሁኔታ የሚያውቁና በ ሃገራቱ ውስጥ ያሉትንም ሆነ በ አካባቢው ሃገራት ያሉትን የ ኢትዮጵያን የ ዲፕሎማሲ በሮች ሲማፀኑ የነበሩት እህቶቻችን ቢናገሩት ይቀላል። የ ኢትዮጵያውቷ ሴት እሮሮም ይሄው ነው። እንዴት ሀገር እንደለለኝ፣ወገን እንደለለኝ፣የተከራከርልኝ አጣሁ? ለምን በ አረብ ምድር ተገፋሁ? ዛሬም የሚሰማ ድምፅ ነው።
”ማርች ስምንት” የ ሴቶች ቀን በዓል በ አረብ ሀገር የመከራ ቀን ለምትገፋው ለ ኢትዮጵያውቷ ሴት የ መራር ፌዝ ያህል ሆኖ ቢሰማት አይፈረደም።የ ዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት የ ”ቬናን” ስምምነት የፈረመችው ሀገር ዜጎች ዛሬም መረር ያለ ዲፕሎማስያዊ እርምጃ ወስዶ” ዘጎቼ ተሰቃዩ” ብሎ የምናገርላቸው መንግስት አጥተው ያለቅሳሉ። የ ሙሴ ግማሽ አካል የነብርሺው እህቴ፣ ንጉስ ሰለሞን የማለለልሽ እናቴ ሳባ ፣ ጣልያኖች ስምሽን ሲሰሙ የምርዱልሽ ጣይቱ፣ ከሁሉም ከሁሉም ያሳደግሽኝ ኢትዮጵያ ዛሬ አስታዋሽ አጥቼ ወድቀልሻለሁ! እያሉ።

No comments:

Post a Comment