Tuesday, March 10, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ኢህአዴግ›› የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ – በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው በላከው ደብዳቤ ‹‹በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም፡፡›› ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው አክሎም ‹‹የግንባሩ ዕጩዎች በሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች የየትኛው አባል ፓርቲን መወከላቸው ሳይገለፅ ‹ኢህአዴግ› ብቻ እየተባሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ‹የህወሓት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ኦህዴድ› አባላትና በተጨባጭም የእነዚህ አራት ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች መሆናቸው እየታወቀ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ በአሳሳች ሁኔታ ‹ኢህአዴግ› በሚባል የአንድ ውህድ ፓፓርቲው በላከው ደብዳቤ ‹‹በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም፡፡›› ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው አክሎም ‹‹የግንባሩ ዕጩዎች በሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች የየትኛው አባል ፓርቲን መወከላቸው ሳይገለፅ ‹ኢህአዴግ› ብቻ እየተባሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ‹የህወሓት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ኦህዴድ› አባላትና በተጨባጭም የእነዚህ አራት ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች መሆናቸው እየታወቀ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ በአሳሳች ሁኔታ ‹ኢህአዴግ› በሚባል የአንድ ውህድ ፓርቲ ዕጩ መስለው ቀርበዋል›› ብሏል፡፡ ይህም ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ህግን ያልተከተለ፣ ወጥነት የሚጎድለውና ህብረተሰቡንም ግራ የሚያጋባ እንዲሁም ለኢህአዴግ ያደላ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ እንደሚያመለክት ገልጾአል፡፡
‹‹ምርጫውን ያስፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ጉልህ ስህተት ሲፈፀም በቸልታ እያለፈ ህገ ወጥነትን እየተባበረ እና እያበረታታ ነው›› ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ የሚባል ግለሰብ አባላት ያሉት ፓርቲ ሳይኖር በስሙ የተመዘገቡት ዕጩዎች በአስቸኳይ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙና ጉዳዩም ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ሲል ምርጫ ቦርድን አሳስቧል፡፡
የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች እንወክላቸዋለን በሚሉት አራቱም ክልሎች ዕጩዎችን በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስም ‹‹ህወሓት-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ብአዴን-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ኦህዴድ-ኢህአዴግ›› እና ‹‹ደኢህዴን-ኢህአዴግ›› በሚል ያስመዘገቡ ሲሆን አዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡ርቲ ዕጩ መስለው ቀርበዋል›› ብሏል፡፡ ይህም ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ህግን ያልተከተለ፣ ወጥነት የሚጎድለውና ህብረተሰቡንም ግራ የሚያጋባ እንዲሁም ለኢህአዴግ ያደላ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ እንደሚያመለክት ገልጾአል፡፡
‹‹ምርጫውን ያስፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ጉልህ ስህተት ሲፈፀም በቸልታ እያለፈ ህገ ወጥነትን እየተባበረ እና እያበረታታ ነው›› ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ የሚባል ግለሰብ አባላት ያሉት ፓርቲ ሳይኖር በስሙ የተመዘገቡት ዕጩዎች በአስቸኳይ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙና ጉዳዩም ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ሲል ምርጫ ቦርድን አሳስቧል፡፡
የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች እንወክላቸዋለን በሚሉት አራቱም ክልሎች ዕጩዎችን በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስም ‹‹ህወሓት-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ብአዴን-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ኦህዴድ-ኢህአዴግ›› እና ‹‹ደኢህዴን-ኢህአዴግ›› በሚል ያስመዘገቡ ሲሆን አዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡11039154_782669048490116_1134843809282896994_n10459922_782669068490114_3327966333789706114_n

የአባይ ግድብ በግብጽ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ መገንባቱ ወያኔ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ያሳያል::

በውጪዉም አለም ቦንድ ለመሸጥ ቢዘምትም ሳይሳካለት ቀርቷል::ሻእቢያ እና በአከባቢው ያሉ ጉዳዮች ወያኔን ውጥረት ውስጥ ጨምረውታል::ይህ የትግሉ አንድ አካል የሆነ የድል ጥርጊያ መንገድ ለፖለቲካ ድል ልንጠቀምበት ይገባል::የአባይ ግድብ ትከትሎ የመልስን መሞት አስታኮ ግለሰቡን አባይን የደፈረ መሪ በማለት እስከማላዘን ተደርሷል::የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንደሚያሳየን ከሆነ የኢትዮጵያ የመጨረሻእ ንጉስ ሃይለስላሴ አባይን ለመገደን ይህንኑ የግድብ ዲዛይን አሰርተው ነው ዲዛይኑ በገንዘብ ኖቶች ላይ ሳይቀር ታትሟል; በጊዜው..ወያኔ ያንን ዲዛይን በዘመናዊ መሃንዲሶች አሻሻለው እንጂ አዲስ ነገር አልፈጠረም::
አባይም ግድብ እንደ ባድመ ድል ለጭፈራ አቀባብሎ እንዳይሰጠን .. መቸም ወያኔ በሰው መቀለድ ለምዷል::የአባይ ቦንድ የገዛህ የገዛሽ ሁሉ ነገሮች ሁሉ ባዶ ጭብጨባ ሆነዋል:: ለሕዝብ የማይጨነቀው ወያኔ በኢኮኖሚ ከደቀቀው የመንግስት ሰራተኘው ጀምሮ እስከ ጎንበስ ቀና ብሎ ደክሞ እስከሚሰራው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ድረስ በአባይ ቦንድ ስም ከፍተኛ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል::
አሁን እየሰማንው ያለነው ደሞ አባይ የሚገደበው ሱዳን እና ግብጽ በፈለጉት መንገድ መሆኑ እየተነገረን ነው:: አስቀድመን እንደተናገርነው የህዝብ መብቶች ሳይረጋገጡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሳይገደቡ ህዝብን በግዳጅ ከጉሮሮው በቦንድ ስም እየነጠቁ ሕዝብ ያተዋጠለትን ሕዝብን ያላሳተፈ ግድብ እገነባለሁ ብሎ መነሳት ከባት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል ይህንንም ኪሳራ እያየነው ነው::ወያኔ ከሱ በላይ አዋቂ እና ከሱ በላይ ልሃገር ለህዝብ ጠበቃ የልማት ቡድን አድርጎ ቢንጠራራም ራሷን ከፍ ከፍ ያደረገች ማሽላ አንድም ለወንጭፍ አንድም ለውፍ .. የሚለውን ያስታውሰናል::
ወያኔ የሰበሰበው ቦንድ ለንግድ ድርጅቶቹ ካፒታል ማሳደጊያ ካደረገው በኋላ እየተሰራ ያለው ስራ ሁሉ በእኩይነት የተከበበ ከመሆኑም ባሻገር በውስጡ ያለውን መፈረካከስ ሙስና እና የፓርቲ ካድሬዎች መበስበስ እንዲሁም የተቃዋሚው ጎራ መጠናከር በጣም ስላሰጋው በተጨማሪም የኤርትራ ጋር ያለው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱ በአባይ ግድብ ላይ ያለው ልፍስፍስ አቋሙ የባሰ ሽባ በመሆኑ እጁን ለግብጽ እና ሱዳን እንዲሰጥ ተገዷል::ከኤርትራ ጋር ጦርነት ብንገጥም ሱዳን እና ግብጽ በተዝዋዋሪ ሊያጠቁን ይችላሉ የሚለው የወያኔ ጭንቀት እንዲሁም ለአባይ ግድብ ያሰበው ሁሉ ሳይሳካ በባዶ ስላስቀረው በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚም በባዶ ካዝና ስለቀረ መጣፊያው ያጠረው ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ የአባይን ግድብ ለግብጽ እና ሱዳን አስረክቧል::አሁንም የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ከአባይ ግድብ በፊት የሰብአዊ መብት ጥሰት ይገደብ::የሰባዊ መብት እና የህዝቦች ነጻነት ባሌለበት አገር በልማት ስም ራስን መቆለል እንደምናየው ውርደቱ በአደባባይ ያጋልጣል::ኢትዮጵያውያን ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን በወያኔ መቃብር ላይ ነጻነታችንን ማረጋገጥ አለብን::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ዘርን ያማከለ ቅነሳ እና በአዲስ የመተካት ስራ ሊጀመር ነው::

በመከላከያ ሰራዊቱ በተለያዩ እዞች ውስጥ የተነሳውን የጥቅማ ጥቅም እና ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ተከትሎ የአማራ እና ኦሮሞ መኮንኖች ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ እንደሚቀነሱ እና በአዲስ እንደሚተኩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:: በየእለቱ ለስብሰባ የሚቀመጠው ሕወሓት መራሹ የጄኔራል መኮንኖች የአንድ ብሄር ቡድን ተጠንቷል ባለው መሰረት በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች የሚፈጠሩት ከአማራው እና ከኦሮሞው ወገን ከሆኑት መኮንኖች ሲሆኑ ይህንንም የሚመሩት የውስጥ መዥገር የሆኑት የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ስለሆኑ ከሰራዊት ውስጥ በመቀነስ በተለያዩ መንገዶች በወንጀል ለማጥመድ እና ከነማን ጋር እንደሚገናኙ አስፈላጊውን የደህንነት ክትትል ማድረግ ይገባል ሲል ተነጋግሮበታል::እነዚህን የሰራዊቱን መኮንኖች በመቀነስ በአዳዲስ እና ታማኝ መኮንኖች መተካት ያስፈልጋል ያለው ስብሰባው አዳዲስ የመኮንንነት ማእረጎች ብዛት ላላቸው ታማኝ መኮንኖች እንደሚሰጥ ጠቁሟል::
በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የለውጥ ጥያቄ ያነሱት መኮንኖች ከተለያዩ የታጠቁ የጠላት ሃይሎች እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በመተባበር የመንግስትን ህልውና እየተፈታተኑት ከመሆኑም ባሻገር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከቀድሞ ስርኣት የተወረሱ እና ለዲሞክራሲው እና ለልማቱ እንቅፋት ስለሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ተብሏል::ከግንቦት ሰባት እና ከተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘት በሰራዊቱ ውስጥ ያለነበሩ እና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በመፍጠር ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ሰዎችን በማስኮብለል መረጃ በማቀበል እንዲሁም አለመተማመን እንዲኖር በመስራት ከፍተኛ ደንቃራ ሆነዋል::የሰራዊቱ የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ እንደገለጹት ተጠና የተባለው ጥናት ለጄኔራል መኮንኖቹ ያልተበተነ ሲሆን የስብሰባው መሪ የሆኑት ኢታማጆር ሹሙ እጅ በመሆን ሰነዱ እየተነበበ የተወያዩበት እና ይህም የሚያመለክተው በሕወሓት ጀኔራሎች መካከልም መተማመን አለመኖሩን ያሳያል ብለዋል::
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/5245#sthash.9fcFuIc2.dpuf

”ማርች 8” እና ኢትዮጵያዊቷ ሴት ዛሬ! – ጉዳያችን


ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረብያ ስደት ላይ
Ethiopian Women in Soudi”ኢትዮጵያዊቷ ሴት ለየት ያሉ ባህርያት አላት። በቅዱሱ መፅሐፍ ላይ ሙሴ ህዝበ አስራኤልን ይዞ ከ ግብፅ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲገባ በስራው ሁሉ የምትረዳው እና ለትዳሩ አጋር ያደረገው ኢትዮጵያዊቷን መሆኑን በቅዱስ መፅሐፍ ውስጥ ማንበቤን አስታውሳለሁ። ‘በምድር ከሚነሱት ነገስታት ማንም ያንተን ያህል ጥበብም ሆነ ሀብት አይኖረውም’ የተባለው ንጉስ ሰለሞን ልቡን ከፍቶ የሆዱን ያወራው ከ ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ (አዜብ) ጋር ነው። ኢትዮጵያውያን ሴቶች ልዩ ናቸው። ክብራቸው፣ዝምታቸው፣እርጋታቸው እና አስተዋይነታቸው ሁሉ የተለየ ድባብ ያላብሳቸዋል ።አዲስ አበባ ለስብሰባም ሆነ ለተመሳሳይ ሥራ ስሄድ ከምገባበት ኬክ ቤት ጀምሮ አስከ አየር መንገዳችሁ አስተናጋጆች ድረስ ያሉት ሴቶችሁ ልዩ፣አስተዋይ እና ብሩህ አእምሮ አላቸው።” ካምፓላ ውስጥ በሚገኘው ”ማካራሬ” ዩንቨርስቲ ውስጥ የ ልማት ጥናት ፕሮፌሰር ዩጋንዳዊው ማተምቤ ናቸው። አዎን ከተናገሩት ውስጥ አንድም የሚጣል እንደሌለው አውቃለሁ። ያንን ንግግር ዛሬ ላይ ሆኘ ሳየው በተለይ” ማርች ስምንት የሴቶች ቀን ታስቦ ዋለ” የሚለው ከኮሚንስቶች ፕሮፓጋንዳ ያላለፈ፣ የወረቀት እና ንግግር ማሳመርያ ዜና መሰል ነገር ከወደ ሀገር ቤት ስሰማ ያስገርመኛል።ይህ ማለት ግን ”ማርች” ስምንት የሴቶች ቀን መከበር የለበትም የሚል ሃሳብ የለለኝ መሆኑን እንዳትዘነጉብኝ።አከባበሩ አንዳች የረባ የሴት እህቶቻችንን ሕይወት የሚያሻሻል ሥራ ተሰርቶ ቢሆን ጥሩ ነበር።ሁኔታው ተቃራኒ ሆኖ ሳለ ስለ በዓሉ ማውራት በራሱ በሴት እህቶቻችን ላይ ከመቀለድ አይተናነስም።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ( UNHCR) ሰኔ 27/2011 አንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ”በ 2011 የ ሰዎች ዝውውር በ ኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ባወጣው ሪፖርት ላይ አንዲህ የሚል ሰፍሮ ይገኛል-
”Young women, most with only three to four years of primary education, from various PARTS of Ethiopia are subjected to domestic servitude throughout the Middle East, as well as in Sudan, and many transit through Djibouti, Egypt, Libya, Somalia, Sudan, or Yemen as they emigrate seeking work. Some women become stranded and exploited in these transit countries, unable to reach their intended destinations. Many Ethiopian women working in domestic service in the Middle East face severe abuses indicative of forced labor, including physical and sexual assault, denial of salary, sleep deprivation, and confinement. Many are driven to despair and mental illness, with some committing suicide…..” 1
”ከ ሦስተኛና አራተኛ ክፍል ያልዘለሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መጥተው ጅቡትን፣ግብፅን ፣ሊብያን፣ሶማልያን፣ሱዳንን ወይንም የመንን አቁአርጠው ወደ መካከለኛው ምስራቅ የ አረብ ሃገራት ለመሄድ ይሞክራሉ።ብዙዎች ገና እነኝህን ሃገራት ሳይሻገሩ እዝያው ጉልበታቸውን ሸጠው እንድያድሩ ያረጋቸዋል….በመካከለኛው ምስራቅ በሥራ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በ ከባድ የ ጉልበት ሥራ፣የ አካልና የ ፆታ ጥቃት፣የለፉበትን የመነጠቅ ወዘተ ይፈፀምባቸዋል።በእ ዚህም ምክንያት ብዙዎች የ አአምሮ ህመም ደርሶባቸው እራሳቸው ያጠፋሉ….”
”እማዬ ለምን ወለድሽኝ ?”
Ethiopian in Saoudiዛሬ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ እህቶቻችን በሊባኖስ፣ሳዑድ አረብያ፣የተባበረው አረብ አምረት፣ኩዌት፣ወዘተ በቤት ውስጥ ሥራ እና በተለያዩ አስከፊ ተግባራት ተሰማርተው ይገኛሉ።አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ እህቶቻችን ለአረብ ሀገር እንግልት ሲሳፈሩ ያገኛሉ። ይህ ብቻ አደለም በቅርቡ በአዲስ አበባው ራድዮ እንደተገለፀው ወደ አረብ ሀገር የሚያሰድዱት ደላሎች ከ ከተሞች ይበልጥ ሰፊ የመገናኛ መረባቸው በገጠር ውስጥ መሆኑ እና ለምሳሌ በወሎ ውስጥ በምትገኝ የአንድ ገበሬ ማህበር መንደር ውስጥ ለ ማህበራዊ ጉዳይ ከተሰበሰቡት ገበሬዎች ለ ናሙና በተወሰደ መረጃ ከ ሃምሳ ገበሬዎች ውስጥ ሰላሳ ሁለቱ ልጆቻቸውን ለ አረብ ሀገር እንግልት መላካቸውን ገልፀዋል። ከእዚህ ሁሉ አሳዛኙ ነገር ደግሞ ሁሉም የ ሴት ልጆቻቸውን ወሬ ሰምተው የማያውቁ መሆናቸውን ና ግራ መጋባታቸውን በለቅሶ መግለፃቸው ነው ። የ እህቶቻችን ጉዞ በ አየርመንገድ ብቻ የምመስለን ካለን በጣም ተሳስተናል። በ እዚሁ የ ራድዮ ዘገባ መሰረት ባለፉት አምስት ወራት ብቻ በ ሱዳን በኩል የወጡት እህቶቻችን ብዛት በ ብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠር መሆኑም ተነግሯል።
በ አረብ ሀገር ያሉት እህቶቻችንን መከራ ና ስቃይ መተንተን በ ቃላት መቀለድ ሆነብኝ።ከፎቅ ላይ እራሳቸውን የወረወሩትን፣መርዝ የጠጡትን፣የፈላ ውሃ የተደፋባቸውን፣ምግብ ሳይበሉ በረሃብ ጠኔ ሕይወታቸው ያለፈውን፣እስር ቤት ተወርውረው ተረስተው የሞቱትን፣ ኩላሊታቸው የቀዶ ጥገና ሕክምና አዋቂ ባልሆኑ ሰዎች ወጥቶ የተወሰደባቸውን (ከዓመት በፊት ‘ሲ ኤን ኤን’ የተሰኘውን የ አሜሪካ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያውያን እህቶቻችን የኩላሊት መወሰድ ላይ ያሳየውን ዘገባ ልብ በሉ) እህቶቻችን ዛሬም ”እማዬ ለምን ወለድሺኝ?” እያሉ ነው።መከራን የምንረዳው እኛ በዝያ መከራ ውስጥ ተገብተን አልያም በእህታችን ወይንም በሴት ልጃችን ላይ ደርሶ ቢሆንስ? ብለን ስናስብ ብቻ ሊሆን ይችላል።
ኢትዮጵያዊት ሴት በአረብ ሃገራት ውስጥ የተዋረደችውን ያህል በታሪካችን የተዋረደችበት (ውርደቱ የ አኔም፣የናንተም፣የሁላችንም መሆኑን ሳንዘነጋ) ጊዜ ነበር ለማለት አያስደፍርም ።በአረባውያኑ ምድር ኢትዮጵያውቷን ሴት አይዞሽ ባይ ማጣት፣ግራ መጋባት፣ተስፋ መቁረጥ፣ግፍ እና መከራው አንገላተዋት ባዶ አውላላ ሜዳ ላይ የቀረች ብቸኛ ፍጥረት የሆነች ያህል እየተሰማት ያለችበት ጊዜ ነው።
142398998551ሀገሮች በድንበር መካለል ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በመካከላቸው የሚኖረውን ግንኙነት ከንግዱ ዘርፍ ባለፈ የ ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር ሌላው የሚያገናኛቸው ጉዳይ ነው። ይህ ግንኙነት ደግሞ ዲፕሎማስያዊ ግኑኝነት እንድያዳብሩ ትልቅ በር ከፍቷል ። ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት በ ዘመናት ውስጥ የራሱን አድገት አያሳየ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሰናል።የ ዲፕሎማሲ ግንኙነት አጅግ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ሲሰራበት የነበረውን ዘመን አልፎ ዛሬ ”public diplomacy” ”ግልፅና ሕዝቡን መሰረት ያደረገ” የ ዲፕሎማሲ ዘመን ላይ እንገናኛለን። የ ሀገሮችን የ ዲፕሎማሲ ግንኙነት መልክ ለማስያዝ ና ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በሁዋላ በ ሀገሮች መካከል የነበረውን ግንኙነት መልክ ያስያዘው ብሎም የ ዓለም አቀፍ ሕግን ቅርፅ የሰጠው አሁንም ድረስ በሥራ ላይ የሚገኘው የ ዲፕሎማሲ ሕግ የ” ቬና ኮንቬንሺን ” (የ ቬና ውል ) ይባላል። ይህ ውል በ ሚያዝያ 18/1961 እንዳውሮፓውያን አቆጣጠር ወጥቶ በ ሚያዝያ 24/1964 አሁንም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ሥራ ላይ ዋለ። በ አውሮፓውቷ ሀገር ኦስትርያ ዋና ከትማ ቬና ውሉ ሲፈረም ከፈረሙት ሀገሮች አንዷ በወቅቱ አብዛኛዎቹ የ አፍሪካ ሀገሮች በ ቅኝ ግዛት ስር በሆኑበት ዘመን ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን የ ውሉ ቀዳሚ ፈራሚ ብቻ ሳትሆን በ ማርቀቅ ሂደቱም ሁሉ ተሳታፊ ነበረች።ዛሬ ግን የእዚህን ውል ዋና አካል የሆነውን አንቀፅ ሶስት የ አትዮጵያ መንግስት ከነመኖሩም የዘነጋው ይመስላል።
የ ቬና ውል አንቀፅ ሶስት ”b” አንዲህ ይላል-
Article 3
1.The functions of a diplomatic mission consist, inter alia, in:
(a) Representing the sending State in the receiving State;
(b) Protecting in the receiving State the interests of the sending State and of its nationals, within the limits permitted by international law; 2
”የ አንድ ሀገር የ ዲፕሎማሲ ሉዑክ አንዱ ተግባር በ ተቀበለው ሀገር ውስጥ የ ሃገሩን ጥቅሞች ና የ ዜጎቹን ጥቅሞች የ አለማቀፍ ሕግ ማቀፍን በተከተለ መንገድ ማስከበር” ነው ይላል።
የሀገራችን የወቅቱ የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስት አባልነትን መሰረት ያደረገ እና ቅድምያ ለመንግስት ታማኘትን ማእከል ያደረገው የሀገራችን ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ስርዓት በመካከለኛው ምስራቅ ለሚሰቃዩት እህቶቻች በቁስል ላይ ቁስል ሆኖባቸዋል።
ዛሬ ለ እህቶቻችን በሄዱበት ሀገር መብታቸውን ለማስከበር ኃላፊነት ያለበት መንግስት መሆኑን የሚዘነጋው አይኖርም ።ይህ ደግሞ በ አለማቀፍ ሕግ እንደ መንግስት ተቁአምነት ግዴታው ነው።የአንድ መንግስት ቀዳሚ ተግባር የ ሃገሩን ሉዓላዊነት ከማስከበር ጀምሮ የ ዜጎቹን ደህንነት (ዜጎቹ በየትኛውም የ ምድር ማአዘን ቢኖሩ) ማስጠበቅ ነው። አሁንም ይህ ኃላፊነት በቀጥታ የምመለከቷ መንግስትን ነው።መንግስት በ አረብ ሀገር እንባዋን የምታፈሰውን ኢትዮጵያዊት ሴት ለመርዳት የወሰደው አርምጃ ትንሿ ጅቡቲ በ ዲፕሎማሲ ተልኮዋ ከምትሰራው ሥራ ያነሰ ነው ሲሉ ብዙዎች ይተቻሉ።ይህም ተራ በስሜታዊነት የተሞላ ነቀፋ ሳይሆን በ ገሃድ የታየ እውነታ ነው። በ ሶርያ፣ሊባኖስ፣ሳዑድ አረብያ፣ሱዳን የነበረውን ሁኔታ የሚያውቁና በ ሃገራቱ ውስጥ ያሉትንም ሆነ በ አካባቢው ሃገራት ያሉትን የ ኢትዮጵያን የ ዲፕሎማሲ በሮች ሲማፀኑ የነበሩት እህቶቻችን ቢናገሩት ይቀላል። የ ኢትዮጵያውቷ ሴት እሮሮም ይሄው ነው። እንዴት ሀገር እንደለለኝ፣ወገን እንደለለኝ፣የተከራከርልኝ አጣሁ? ለምን በ አረብ ምድር ተገፋሁ? ዛሬም የሚሰማ ድምፅ ነው።
”ማርች ስምንት” የ ሴቶች ቀን በዓል በ አረብ ሀገር የመከራ ቀን ለምትገፋው ለ ኢትዮጵያውቷ ሴት የ መራር ፌዝ ያህል ሆኖ ቢሰማት አይፈረደም።የ ዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት የ ”ቬናን” ስምምነት የፈረመችው ሀገር ዜጎች ዛሬም መረር ያለ ዲፕሎማስያዊ እርምጃ ወስዶ” ዘጎቼ ተሰቃዩ” ብሎ የምናገርላቸው መንግስት አጥተው ያለቅሳሉ። የ ሙሴ ግማሽ አካል የነብርሺው እህቴ፣ ንጉስ ሰለሞን የማለለልሽ እናቴ ሳባ ፣ ጣልያኖች ስምሽን ሲሰሙ የምርዱልሽ ጣይቱ፣ ከሁሉም ከሁሉም ያሳደግሽኝ ኢትዮጵያ ዛሬ አስታዋሽ አጥቼ ወድቀልሻለሁ! እያሉ።